-
ዘኁልቁ 32:39አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
39 የምናሴ ልጅ የማኪር+ ልጆች በጊልያድ ላይ ዘምተው ምድሪቱን ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አስወጧቸው።
-
-
ኢያሱ 13:29-31አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 በተጨማሪም ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኸውም ለግማሹ የምናሴ ነገድ በየቤተሰባቸው ርስት ሰጠ።+ 30 ግዛታቸውም ከማሃናይም+ አንስቶ ያለው ሲሆን ባሳንን በሙሉ፣ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ፣ በባሳን የሚገኙትን የያኢር+ የድንኳን ሰፈሮች በሙሉ፣ 60 ከተሞችን ያጠቃልላል። 31 የጊልያድ እኩሌታ እንዲሁም በባሳን የሚገኙት የኦግ ንጉሣዊ ግዛት ከተሞች ማለትም አስታሮትና ኤድራይ+ የምናሴ ልጅ ለሆነው ለማኪር+ ልጆች ይኸውም ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየቤተሰባቸው ተሰጡ።
-