ዘዳግም 31:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው+ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ*+ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።+ ነህምያ 9:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 የተመሸጉ ከተሞችንና+ ለም የሆነውን* መሬት ያዙ፤+ መልካም ነገሮች ሁሉ የሞሉባቸውን ቤቶች፣ የተቆፈሩ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶችን፣ የወይን እርሻዎችን፣ የወይራ ዛፎችንና+ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የፍራፍሬ ዛፎች ወረሱ። በመሆኑም እስኪጠግቡ ድረስ በሉ፤ ሰቡም፤ ታላቅ በሆነው ጥሩነትህም ተንደላቀቁ።
20 ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው+ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ*+ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።+
25 የተመሸጉ ከተሞችንና+ ለም የሆነውን* መሬት ያዙ፤+ መልካም ነገሮች ሁሉ የሞሉባቸውን ቤቶች፣ የተቆፈሩ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶችን፣ የወይን እርሻዎችን፣ የወይራ ዛፎችንና+ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የፍራፍሬ ዛፎች ወረሱ። በመሆኑም እስኪጠግቡ ድረስ በሉ፤ ሰቡም፤ ታላቅ በሆነው ጥሩነትህም ተንደላቀቁ።