-
ዘዳግም 3:4, 5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚያም ከተሞቹን በሙሉ ያዝን። ከእነሱ ያልወሰድነው አንድም ከተማ አልነበረም፤ በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኘውን የአርጎብን ክልል በሙሉ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰድን።+ 5 እነዚህ ከተሞች በሙሉ በረጃጅም ቅጥሮች የታጠሩ እንዲሁም በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸው ነበሩ፤ ከእነዚህም በተጨማሪ በጣም ብዙ የገጠር ከተሞች ነበሩ።
-