ዘኁልቁ 27:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ካየኸውም በኋላ እንደ ወንድምህ እንደ አሮን+ አንተም ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ፤*+ 14 ምክንያቱም ማኅበረሰቡ በጺን ምድረ በዳ ከእኔ ጋር በተጣላ ጊዜ ከውኃዎቹ ጋር በተያያዘ በፊታቸው ሳትቀድሱኝ በመቅረታችሁ ትእዛዜን ተላልፋችኋል።+ እነዚህም በጺን ምድረ በዳ+ በቃዴስ+ የሚገኙት የመሪባ ውኃዎች+ ናቸው።” ዘዳግም 3:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ጲስጋ አናት ውጣና+ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ተመልከት።+ ዘዳግም 34:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’+ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።”+ 5 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴም ልክ ይሖዋ እንደተናገረው በዚያው በሞዓብ ምድር ሞተ።+
13 ካየኸውም በኋላ እንደ ወንድምህ እንደ አሮን+ አንተም ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ፤*+ 14 ምክንያቱም ማኅበረሰቡ በጺን ምድረ በዳ ከእኔ ጋር በተጣላ ጊዜ ከውኃዎቹ ጋር በተያያዘ በፊታቸው ሳትቀድሱኝ በመቅረታችሁ ትእዛዜን ተላልፋችኋል።+ እነዚህም በጺን ምድረ በዳ+ በቃዴስ+ የሚገኙት የመሪባ ውኃዎች+ ናቸው።”
4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’+ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።”+ 5 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴም ልክ ይሖዋ እንደተናገረው በዚያው በሞዓብ ምድር ሞተ።+