19 አባቱ ግን “አውቄአለሁ ልጄ፣ አውቄአለሁ። እሱም ቢሆን ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል። ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከእሱ የበለጠ ይሆናል፤+ ዘሩም በዝቶ ብዙ ብሔር ለመሆን ይበቃል”+ በማለት እንቢ አለው። 20 በመሆኑም በዚያው ቀን እንዲህ ሲል እነሱን መባረኩን ቀጠለ፦+
“እስራኤል በአንተ ስም እንዲህ በማለት ይባርክ፦
‘አምላክ እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርግህ።’”
በዚህ ሁኔታ ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።