-
ዘፀአት 18:17, 18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 በዚህ ጊዜ የሙሴ አማት እንዲህ አለው፦ “እያደረግክ ያለኸው ነገር መልካም አይደለም። 18 ይህ ሥራ ለአንተ ከባድ ሸክም ስለሚሆን አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያለው ይህ ሕዝብ መድከማችሁ አይቀርም፤ ደግሞም ብቻህን ልትሸከመው አትችልም።
-
-
ዘኁልቁ 11:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “አገልጋይህን የምታጎሳቁለው ለምንድን ነው? በፊትህ ሞገስ ያጣሁትና የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ የጫንከው ለምንድን ነው?+
-
-
ዘኁልቁ 20:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ሕዝቡም እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣላ፦+ “ምነው ወንድሞቻችን በይሖዋ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ሞተን ባረፍነው ኖሮ!
-