የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 4:25, 26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 “ልጆችና የልጅ ልጆች ስታፈሩ፣ በምድሪቱም ላይ ረጅም ዘመን ስትኖሩ፣ የጥፋት ጎዳና ወደመከተል ዞር ብትሉና የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል+ ብትሠሩ እንዲሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ክፉ ነገር በመፈጸም እሱን ብታስቆጡት+ 26 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ያለጥርጥር ወዲያውኑ እንደምትደመሰሱ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምሥክር አድርጌ እጠራባችኋለሁ። በምድሪቱ ላይ ረጅም ዘመን ከመኖር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳላችሁ።+

  • ዘዳግም 30:17, 18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 “ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና+ ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው+ 18 በእርግጥ እንደምትጠፉ+ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል።

  • ኢያሱ 23:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “ይሁንና ወደ ኋላ ዞር ብትሉና ከእነዚህ ብሔራት መካከል ተርፈው ከእናንተ ጋር ከቀሩት+ ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ብትመሠርቱ፣ በጋብቻ ብትዛመዱ+ እንዲሁም እናንተ ከእነሱ ጋር ብትወዳጁ፣ እነሱም ከእናንተ ጋር ወዳጅነት ቢመሠርቱ 13 አምላካችሁ ይሖዋ ከዚህ በኋላ ለእናንተ ሲል እነዚህን ብሔራት እንደማያባርራቸው* በእርግጥ እወቁ።+ እነሱም አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር ላይ እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድ፣ አሽክላ፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ እንዲሁም በዓይናችሁ ውስጥ እንዳለ እሾህ ይሆኑባችኋል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ