-
ዘፀአት 19:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 የቀንደ መለከቱም ድምፅ ይበልጥ እየጨመረ ሲመጣ ሙሴ ተናገረ፤ የእውነተኛውም አምላክ ድምፅ መለሰለት።
-
-
ዘዳግም 4:10-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 በኮሬብ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት በቆማችሁበት ቀን ይሖዋ ‘በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት+ ይማሩና ልጆቻቸውንም ያስተምሩ+ ዘንድ ቃሌን እንዲሰሙ+ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ’ ብሎኝ ነበር።
11 “በመሆኑም እናንተ መጥታችሁ በተራራው ግርጌ ቆማችሁ፤ ተራራውም እስከ ሰማያት ድረስ* እየነደደ ነበር፤ ጨለማ፣ ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ነበር።+ 12 ይሖዋም ከእሳቱ ውስጥ ያነጋግራችሁ ጀመር።+ እናንተም ድምፅ ከመስማት በስተቀር መልክ አላያችሁም፤+ የሰማችሁት ድምፅ ብቻ ነበር።+ 13 እሱም እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት* ገለጸላችሁ።+ ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።+
-