ዘፀአት 21:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ዕብራዊ ባሪያ ከገዛህ+ ለስድስት ዓመት ባሪያ ሆኖ ያገለግልሃል፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ያለምንም ክፍያ ነፃ ይወጣል።+ ዘሌዋውያን 25:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 “‘በአቅራቢያህ የሚኖር ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ለአንተ ለመሸጥ ቢገደድ+ እንደ ባሪያ እንዲሠራ አታስገድደው።+