-
ዘዳግም 12:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።+ 6 የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣+ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣+ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን+ እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት+ የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው። 7 እናንተም ሆናችሁ ቤተሰቦቻችሁ በዚያ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ብሉ፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለባረካችሁ በሥራችሁ ሁሉ ተደሰቱ።+
-