-
ዘኁልቁ 18:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ መዋጮ አድርጎ ለይሖዋ የሚያዋጣውን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ ውርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። እኔም ‘በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም’ ያልኳቸው ለዚህ ነው።”+
-
-
ዘዳግም 10:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ድርሻ ወይም ርስት ያልተሰጠው ለዚህ ነው። አምላክህ ይሖዋ በነገረው መሠረት ይሖዋ ርስቱ ነው።+
-
-
1 ቆሮንቶስ 9:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑት ሰዎች ከቤተ መቅደስ የሚያገኙትን ምግብ እንደሚመገቡ እንዲሁም ዘወትር በመሠዊያው የሚያገለግሉ ከመሠዊያው የራሳቸውን ድርሻ እንደሚያገኙ አታውቁም?+
-