-
ዘዳግም 13:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 “አንድ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ከመካከልህ ተነስቶ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር እንደሚያሳይ ቢነግርህና 2 የነገረህ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር ቢፈጸም፣ እሱም ‘ሌሎች አማልክትን እንከተል’ ይኸውም አንተ የማታውቃቸውን አማልክት እንከተል፤ ‘እናገልግላቸውም’ ቢልህ፣ 3 የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል እንዳትሰማ፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* አምላካችሁን ይሖዋን ትወዱት+ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ እየፈተናችሁ ነው።+ 4 እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ።+ 5 ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ግን ይገደል፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ዞር እንድትሉ፣ ከግብፅ ምድር ባወጣችሁና ከባርነት ቤት በታደጋችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እንድታምፁ አበረታቷችኋል። አንተም ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።+
-
-
ኤርምያስ 28:11-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ከዚያም ሃናንያህ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ልክ እንዲሁ እኔም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነጾርን ቀንበር ከብሔራት ሁሉ አንገት ላይ እሰብራለሁ።’”+ ነቢዩ ኤርምያስም ትቶት ሄደ።
12 ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ከሰበረው በኋላ ይህ የይሖዋ መልእክት ወደ ኤርምያስ መጣ፦ 13 “ሄደህ ሃናንያህን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የእንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤+ ይሁንና በእሱ ምትክ የብረት ቀንበር ትሠራለህ።” 14 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እንዲያገለግሉ በእነዚህ ሁሉ ብሔራት አንገት ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነሱም ያገለግሉታል።+ የዱር አራዊትንም እንኳ እሰጠዋለሁ።”’”+
15 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩ ሃናንያህን+ እንዲህ አለው፦ “ሃናንያህ ሆይ፣ እባክህ ስማ! ይሖዋ ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።+ 16 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ። በይሖዋ ላይ ዓመፅ ስላነሳሳህ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’”+
17 በመሆኑም ነቢዩ ሃናንያህ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።
-