የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 34:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እነሱ አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር በሚፈጽሙበትና ለአማልክታቸው በሚሠዉበት+ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ አንተን መጋበዙ አይቀርም፣ አንተም ካቀረበው መሥዋዕት ትበላለህ።+

  • ዘዳግም 7:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል፤+ ከዚያም የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ አንተንም ወዲያው ያጠፋሃል።+

  • ኢያሱ 23:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “ይሁንና ወደ ኋላ ዞር ብትሉና ከእነዚህ ብሔራት መካከል ተርፈው ከእናንተ ጋር ከቀሩት+ ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ብትመሠርቱ፣ በጋብቻ ብትዛመዱ+ እንዲሁም እናንተ ከእነሱ ጋር ብትወዳጁ፣ እነሱም ከእናንተ ጋር ወዳጅነት ቢመሠርቱ 13 አምላካችሁ ይሖዋ ከዚህ በኋላ ለእናንተ ሲል እነዚህን ብሔራት እንደማያባርራቸው* በእርግጥ እወቁ።+ እነሱም አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር ላይ እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድ፣ አሽክላ፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ እንዲሁም በዓይናችሁ ውስጥ እንዳለ እሾህ ይሆኑባችኋል።+

  • ኢሳይያስ 2:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 አንተ ሕዝብህን ይኸውም የያዕቆብን ቤት ትተሃል፤+

      ምክንያቱም እነሱ ከምሥራቅ በመጡ ነገሮች ተሞልተዋል፤

      እንደ ፍልስጤማውያን የአስማት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤+

      በባዕድ አገር ሰዎች ልጆችም ተጥለቅልቀዋል።

  • 1 ቆሮንቶስ 5:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁም?+

  • 1 ቆሮንቶስ 15:33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ