-
ኢሳይያስ 26:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 እነሆ፣ ይሖዋ የምድሪቱ ነዋሪ የፈጸመውን በደል ለመፋረድ
ከመኖሪያ ቦታው ይመጣልና፤
ምድሪቱም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤
በላይዋም የተገደሉትን ከዚህ በኋላ አትደብቅም።”
-
-
ኤርምያስ 26:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 ከገደላችሁኝ በራሳችሁ፣ በዚህች ከተማና በነዋሪዎቿ ላይ የንጹሕ ሰው ደም ዕዳ እንደምታመጡ በእርግጥ እወቁ፤ ይህን ሁሉ ቃል በጆሯችሁ እንድናገር የላከኝ በእርግጥ ይሖዋ ነውና።”
-