የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 26
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤርምያስን ‘እንገድልሃለን’ ብለው ዛቱበት (1-15)

      • ኤርምያስ ከሞት ተረፈ (16-19)

        • የሚክያስ ትንቢት ተጠቀሰ (18)

      • ነቢዩ ዑሪያህ (20-24)

ኤርምያስ 26:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:34፤ 2ዜና 36:4፤ ኤር 25:1፤ 35:1፤ 36:1

ኤርምያስ 26:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለመስገድ።”

  • *

    ወይም “ወደ ይሖዋ ቤት ለሚመጡት፣ በይሁዳ ከተሞች ለሚኖሩት።”

ኤርምያስ 26:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ባሰብኩት ጥፋት እጸጸታለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 55:7፤ ኤር 18:7, 8፤ 36:3፤ ሕዝ 18:27

ኤርምያስ 26:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”

ኤርምያስ 26:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:13, 14፤ ኤር 7:12-14፤ 25:3

ኤርምያስ 26:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 78:60
  • +ኤር 24:9

ኤርምያስ 26:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 26:2

ኤርምያስ 26:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:10

ኤርምያስ 26:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 18:19, 20
  • +ኤር 38:4

ኤርምያስ 26:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:17

ኤርምያስ 26:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በተናገረው ጥፋት ይጸጸታል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:3፤ 36:3፤ ሕዝ 18:32፤ ዮናስ 3:9

ኤርምያስ 26:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤተ መቅደሱም።”

  • *

    ወይም “በዛፍ የተሸፈነ ተረተር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 1:1
  • +2ዜና 29:1
  • +መዝ 79:1፤ ኤር 9:11
  • +ሚክ 3:12

ኤርምያስ 26:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በነበረው ጥፋት አልተጸጸተም?”

  • *

    ወይም “በነፍሳችን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:26

ኤርምያስ 26:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:20, 60፤ 18:11, 14፤ 1ሳሙ 7:2

ኤርምያስ 26:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:34፤ 2ዜና 36:5
  • +2ዜና 16:10

ኤርምያስ 26:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 36:11, 12

ኤርምያስ 26:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:30

ኤርምያስ 26:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:10
  • +2ነገ 22:12, 13፤ ኤር 39:13, 14፤ 40:5
  • +1ነገ 18:4

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 26:12ነገ 23:34፤ 2ዜና 36:4፤ ኤር 25:1፤ 35:1፤ 36:1
ኤር. 26:3ኢሳ 55:7፤ ኤር 18:7, 8፤ 36:3፤ ሕዝ 18:27
ኤር. 26:52ነገ 17:13, 14፤ ኤር 7:12-14፤ 25:3
ኤር. 26:6መዝ 78:60
ኤር. 26:6ኤር 24:9
ኤር. 26:7ኤር 26:2
ኤር. 26:10ኤር 36:10
ኤር. 26:11ኤር 18:19, 20
ኤር. 26:11ኤር 38:4
ኤር. 26:12ኤር 1:17
ኤር. 26:13ኤር 7:3፤ 36:3፤ ሕዝ 18:32፤ ዮናስ 3:9
ኤር. 26:18ሚክ 1:1
ኤር. 26:182ዜና 29:1
ኤር. 26:18መዝ 79:1፤ ኤር 9:11
ኤር. 26:18ሚክ 3:12
ኤር. 26:192ዜና 32:26
ኤር. 26:20ኢያሱ 15:20, 60፤ 18:11, 14፤ 1ሳሙ 7:2
ኤር. 26:212ነገ 23:34፤ 2ዜና 36:5
ኤር. 26:212ዜና 16:10
ኤር. 26:22ኤር 36:11, 12
ኤር. 26:23ኤር 2:30
ኤር. 26:242ነገ 22:10
ኤር. 26:242ነገ 22:12, 13፤ ኤር 39:13, 14፤ 40:5
ኤር. 26:241ነገ 18:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 26:1-24

ኤርምያስ

26 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ ቃል ከይሖዋ ዘንድ መጣ፦ 2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ ቆመህ፣ ለአምልኮ* ወደ ይሖዋ ቤት ስለሚመጡት፣ በይሁዳ ከተሞች ስለሚኖሩት* ሰዎች ሁሉ ተናገር። የማዝህን ቃል ሁሉ ንገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታስቀር። 3 ምናልባት ይሰሙና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በክፉ ሥራቸው የተነሳ በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።*+ 4 እንዲህ በላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የማትሰሙኝና የሰጠኋችሁን ሕግ* የማትከተሉ ከሆነ፣ 5 እንዲሁም ደግሜ ደጋግሜ* ወደ እናንተ የላክኋቸውን፣ እናንተ ያልሰማችኋቸውን የአገልጋዮቼን የነቢያትን ቃል የማትቀበሉ ከሆነ፣+ 6 ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤+ ይህችንም ከተማ ለምድር ብሔራት ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’”’”+

7 ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ሁሉ ኤርምያስ በይሖዋ ቤት ይህን ቃል ሲናገር ሰሙ።+ 8 በመሆኑም ኤርምያስ፣ ይሖዋ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲናገር ያዘዘውን ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ሁሉ ይዘው እንዲህ አሉት፦ “አንተ በእርግጥ ትሞታለህ። 9 ‘ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፤ ይህችም ከተማ ወድማ ሰው አልባ ትሆናለች’ ብለህ በይሖዋ ስም የተነበይከው ለምንድን ነው?” ሕዝቡም ሁሉ በይሖዋ ቤት በኤርምያስ ዙሪያ ተሰበሰበ።

10 የይሁዳ መኳንንት ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ከንጉሡ ቤት* ወደ ይሖዋ ቤት መጥተው በይሖዋ ቤት ባለው በአዲሱ በር መግቢያ ተቀመጡ።+ 11 ካህናቱና ነቢያቱ፣ ለመኳንንቱና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በሞት ሊቀጣ ይገባዋል፤+ ምክንያቱም በገዛ ጆሯችሁ እንደሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯል።”+

12 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ለመኳንንቱ ሁሉና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የሰማችሁትን ቃል ሁሉ በዚህ ቤትና በዚህች ከተማ ላይ እንድተነብይ የላከኝ ይሖዋ ነው።+ 13 እንግዲያው አሁን መንገዳችሁንና ድርጊታችሁን አስተካክሉ፤ የአምላካችሁንም የይሖዋን ቃል ስሙ፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ አመጣዋለሁ ብሎ የተናገረውን ጥፋት ይተወዋል።*+ 14 እኔ ግን በእጃችሁ ነኝ። መልካምና ትክክል መስሎ የታያችሁን ነገር ሁሉ አድርጉብኝ። 15 ከገደላችሁኝ በራሳችሁ፣ በዚህች ከተማና በነዋሪዎቿ ላይ የንጹሕ ሰው ደም ዕዳ እንደምታመጡ በእርግጥ እወቁ፤ ይህን ሁሉ ቃል በጆሯችሁ እንድናገር የላከኝ በእርግጥ ይሖዋ ነውና።”

16 በዚህ ጊዜ መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ ካህናቱንና ነቢያቱን “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በይሖዋ ስም ስለሆነ በሞት ሊቀጣ አይገባውም” አሏቸው።

17 በተጨማሪም በምድሪቱ ከሚኖሩ ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ተነስተው ለተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አሉ፦ 18 “የሞረሸቱ ሚክያስ+ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤

ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+

የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።”’+

19 “ታዲያ በዚያ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉት? ይልቁንም ይሖዋን ፈርቶ፣ ይሖዋ እንዲራራለት አልተማጸነም? ከዚህስ የተነሳ ይሖዋ በእነሱ ላይ ሊያመጣ አስቦት የነበረውን ጥፋት አልተወውም?*+ እኛ ግን በራሳችን* ላይ ጥፋት እየጋበዝን ነው።

20 “ደግሞም በይሖዋ ስም ትንቢት የሚናገር ሌላ ሰው ነበር፤ እሱም የቂርያትየአሪም+ ሰው የሆነው የሸማያህ ልጅ ዑሪያህ ሲሆን ኤርምያስ የተናገረውን ዓይነት ቃል በመናገር በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ተንብዮአል። 21 ንጉሥ ኢዮዓቄም፣+ ኃያል ተዋጊዎቹ ሁሉና መኳንንቱ ሁሉ እሱ የተናገረውን ቃል ሰሙ፤ ንጉሡም ሊገድለው ፈለገ።+ ዑሪያህ ይህን እንደሰማ በጣም ስለፈራ ሸሽቶ ወደ ግብፅ ሄደ። 22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ኢዮዓቄም የአክቦርን ልጅ ኤልናታንን+ እንዲሁም ከእሱ ጋር ሌሎች ሰዎችን ወደ ግብፅ ላከ። 23 እነሱም ዑሪያህን ከግብፅ አምጥተው ወደ ንጉሥ ኢዮዓቄም ወሰዱት፤ እሱም በሰይፍ መትቶ ገደለው፤+ አስከሬኑንም ተራ ሰዎች በሚቀበሩበት ስፍራ ጣለው።”

24 ይሁንና የሳፋን+ ልጅ አኪቃም+ ኤርምያስን ረዳው፤ በመሆኑም ኤርምያስ እንዲገደል ለሕዝቡ አልተሰጠም።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ