-
ዘዳግም 21:18-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 “አንድ ሰው እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው ልጁም አባቱንም ሆነ እናቱን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ቢል፣+ እነሱም እርማት ሊሰጡት ቢሞክሩና እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ ባይሆን+ 19 አባትና እናቱ እሱ ባለበት ከተማ በር ላይ ወዳሉት ሽማግሌዎች ያምጡት፤ 20 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና+ ሰካራም+ ነው’ ይበሏቸው። 21 ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ።+
-
-
ምሳሌ 20:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 አባቱንና እናቱን የሚረግም ሁሉ
ጨለማ ሲሆን መብራቱ ይጠፋበታል።+
-