ዘዳግም 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እናንተም ሆናችሁ ቤተሰቦቻችሁ በዚያ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ብሉ፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለባረካችሁ በሥራችሁ ሁሉ ተደሰቱ።+ ነህምያ 9:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ሌላው ቀርቶ በራሳቸው መንግሥት ሥር በሚተዳደሩበት፣ አትረፍርፈህ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች በሚደሰቱበት እንዲሁም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም* ምድር በሚኖሩበት ጊዜም እንኳ አንተን አላገለገሉም፤+ ከመጥፎ ተግባራቸውም አልተቆጠቡም።
35 ሌላው ቀርቶ በራሳቸው መንግሥት ሥር በሚተዳደሩበት፣ አትረፍርፈህ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች በሚደሰቱበት እንዲሁም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም* ምድር በሚኖሩበት ጊዜም እንኳ አንተን አላገለገሉም፤+ ከመጥፎ ተግባራቸውም አልተቆጠቡም።