ዘፀአት 24:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ።+ ሕዝቡም “ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸምና ለመታዘዝ ፈቃደኞች ነን” አሉ።+ ዘዳግም 31:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል።