ዘፀአት 19:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ‘እናንተን በንስር ክንፎች ተሸክሜ+ ወደ እኔ ለማምጣት ስል በግብፃውያን ላይ ያደረግኩትን ሁሉ እናንተው ራሳችሁ አይታችኋል።+ ኢያሱ 24:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በኋላም ሙሴንና አሮንን ላክኋቸው፤+ ግብፅንም በመካከላቸው በፈጸምኩት ነገር በመቅሰፍት መታኋት፤+ ከዚያም እናንተን አወጣኋችሁ።