21 የሄቤር ሚስት ኢያዔል ግን የድንኳን ካስማና መዶሻ ወሰደች። ከዚያም ሲሳራ ደክሞት ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዶት ሳለ በቀስታ ወደ እሱ ሄዳ ካስማውን ሰሪሳራዎቹ ላይ በመቸንከር ከመሬት ጋር አጣበቀችው። እሱም ሞተ።+
22 ባርቅ ሲሳራን እያሳደደ ወደዚያ አካባቢ ሄደ፤ ኢያዔልም እሱን ለማግኘት ወጣች፤ ከዚያም “ና፣ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። እሱም ከእሷ ጋር ወደ ውስጥ ገባ፤ ሲሳራንም ካስማው ሰሪሳራዎቹ ላይ እንደተቸነከረ ሞቶ አገኘው።