8 የይሖዋን ታቦት ወስዳችሁ ሠረገላው ላይ አስቀምጡት፤ እንዲሁም ለእሱ የበደል መባ አድርጋችሁ የምትልኳቸውን የወርቅ ምስሎች በሣጥን አድርጋችሁ ታቦቱ አጠገብ አስቀምጡ።+ ከዚያም መንገዱን ይዞ እንዲሄድ ላኩት፤ 9 ልብ ብላችሁም ተመልከቱ፦ ታቦቱ ወደ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ+ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከሄደ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እሱ ነው ማለት ነው። ካልሆነ ግን የእሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን፤ ይህ የደረሰብንም እንዲያው በአጋጣሚ ነው።”