11 እንዲህ አላቸው፦ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው ንጉሥ እንዲህ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት አለው፦+ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ+ ሠረገላው ውስጥ ያስቀምጣቸዋል፤+ ፈረሰኞችም+ ያደርጋቸዋል፤ የተወሰኑትንም ከሠረገሎቹ ፊት ፊት እንዲሮጡ ያደርጋል። 12 ለራሱም የሺህ አለቆችንና+ የሃምሳ አለቆችን+ ይሾማል፤ አንዳንዶቹም መሬቱን ያርሳሉ፣+ እህሉን ያጭዳሉ+ እንዲሁም የጦር መሣሪያዎቹንና ለሠረገሎቹ+ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይሠራሉ።