-
1 ዜና መዋዕል 21:24-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ይሁን እንጂ ንጉሥ ዳዊት ኦርናንን እንዲህ አለው፦ “በፍጹም አይሆንም! ሙሉውን ዋጋ ሰጥቼ እገዛዋለሁ፤ ምክንያቱም የአንተ የሆነውን ነገር ወስጄ ለይሖዋ አልሰጥም ወይም ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም።”+ 25 በመሆኑም ዳዊት የቦታውን ዋጋ 600 የወርቅ ሰቅል* መዝኖ ለኦርናን ሰጠው። 26 ዳዊትም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ+ ሠርቶ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና የኅብረት መሥዋዕቶች አቀረበ፤ የይሖዋንም ስም ጠራ፤ እሱም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማያት በእሳት+ መለሰለት። 27 ከዚያም ይሖዋ መልአኩን+ ሰይፉን ወደ ሰገባው እንዲመልስ አዘዘው። 28 በዚህ ጊዜ ዳዊት፣ ይሖዋ በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ መልስ እንደሰጠው ባየ ጊዜ በዚያ ቦታ ላይ መሥዋዕት ማቅረቡን ቀጠለ።
-