24 ሆኖም ንጉሡ አረውናን “በፍጹም አይሆንም! ዋጋውን ልከፍልህ ይገባል። ደግሞም ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር ለአምላኬ ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” አለው። ስለዚህ ዳዊት አውድማውንና ከብቶቹን በ50 የብር ሰቅል ገዛ።+ 25 ዳዊትም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ+ ሠርቶ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረበ። ይሖዋም ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ልመና ሰማ፤+ በእስራኤል ላይ ይወርድ የነበረው መቅሰፍትም ቆመ።