-
2 ዜና መዋዕል 1:3-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ከዚያም ሰለሞንና መላው ጉባኤ በገባኦን+ ወደሚገኘው ኮረብታ ሄዱ፤ ምክንያቱም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእውነተኛው አምላክ የመገናኛ ድንኳን የሚገኘው በዚያ ነበር። 4 ይሁን እንጂ ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከቂርያትየአሪም+ እሱ ወዳዘጋጀለት ስፍራ አምጥቶት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ድንኳን ተክሎለት ነበር።+ 5 የሁር ልጅ የዖሪ ልጅ ባስልኤል+ የሠራው የመዳብ መሠዊያ+ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ይገኝ ነበር፤ ሰለሞንና ጉባኤውም በመሠዊያው ፊት ይጸልዩ ነበር።* 6 ሰለሞንም በዚያ በይሖዋ ፊት መባ አቀረበ፤ በመገናኛው ድንኳን በሚገኘው የመዳብ መሠዊያ ላይ 1,000 የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረበ።+
-