2 “እንግዲህ እኔ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ+ የወለደውን ባስልኤልን+ መርጬዋለሁ። 3 ደግሞም ጥበብ፣ ማስተዋልና እውቀት በመስጠት በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ የተካነ እንዲሆን በአምላክ መንፈስ እሞላዋለሁ፤ 4 ይህን የማደርገው የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ፣ በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣ 5 ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ+ እንዲሁም ከእንጨት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው።+