የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 12:2, 3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩባቸው የነበሩትን ቦታዎች በሙሉ፣ በረጃጅም ተራሮችም ሆነ በኮረብቶች ላይ ወይም በተንዠረገጉ ዛፎች ሥር ያሉትን ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ አጥፉ።+ 3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+

  • ኢሳይያስ 57:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 በትላልቅ ዛፎች መካከል፣

      ቅጠሉ በተንዠረገገም ዛፍ ሥር ሁሉ በስሜት የተቃጠላችሁ፣+

      በሸለቆዎች* ውስጥ፣ በቋጥኞች መካከል

      ልጆችን የምታርዱ አይደላችሁም?+

  • ኤርምያስ 2:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤+

      የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ።

      አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤

      ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይና ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር+

      ለማመንዘር ተንጋለሽ ተኝተሻልና።+

  • ሆሴዕ 4:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 በተራሮች አናት ላይ ይሠዋሉ፤+

      ደግሞም በኮረብቶች ላይ

      እንዲሁም በባሉጥ ዛፎች፣ በሊብነህ ዛፎችና* በትልቅ ዛፍ ሁሉ ሥር የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤+

      ምክንያቱም የዛፎቹ ጥላ መልካም ነው።

      ከዚህም የተነሳ ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* ይሆናሉ፤

      ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ