የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • እስራኤል ይሖዋን ትታ ሌሎች አማልክትን ተከተለች (1-37)

        • እስራኤል በባዕድ የወይን ተክል ተመሰለች (21)

        • ልብሶቿ በደም ቆሽሸዋል (34)

ኤርምያስ 2:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ታማኝ ፍቅር ታሳዪ እንደነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 2:15
  • +ዘፀ 24:3
  • +ዘዳ 2:7

ኤርምያስ 2:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:6፤ ዘዳ 7:6
  • +ዘፀ 17:8, 13

ኤርምያስ 2:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:21
  • +መዝ 115:4, 8
  • +ኢሳ 5:4፤ ሚክ 6:3

ኤርምያስ 2:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 14:30
  • +ዘዳ 1:1፤ 32:9, 10
  • +ዘዳ 8:14, 15

ኤርምያስ 2:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:26, 27፤ ዘዳ 6:10, 11፤ 8:7-9
  • +ዘሌ 18:24፤ ዘኁ 35:33፤ መዝ 78:58፤ 106:38፤ ኤር 16:18

ኤርምያስ 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:12፤ ሰቆ 4:13
  • +ሕዝ 34:7, 8
  • +1ነገ 18:19፤ ኤር 23:13

ኤርምያስ 2:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 20:35፤ ሚክ 6:2

ኤርምያስ 2:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደሴቶች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:2, 4
  • +ዘፍ 25:13፤ መዝ 120:5፤ ኤር 49:28

ኤርምያስ 2:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:20

ኤርምያስ 2:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈልፍለዋል።” ከዓለት ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 36:9፤ ኤር 17:13፤ ራእይ 22:1

ኤርምያስ 2:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:29፤ ኤር 4:7

ኤርምያስ 2:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሜምፊስና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 46:19
  • +ኤር 43:4, 7፤ 46:14፤ ሕዝ 30:18

ኤርምያስ 2:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:9፤ 2ዜና 7:19, 20

ኤርምያስ 2:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከአባይ ወንዝ ተገንጥሎ የሚፈሰውን ውኃ ያመለክታል።

  • *

    ኤፍራጥስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:2፤ 31:1፤ ሰቆ 5:6፤ ሕዝ 16:26፤ 17:15
  • +2ነገ 16:7፤ ሆሴዕ 5:13

ኤርምያስ 2:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:18
  • +ኤር 5:22

ኤርምያስ 2:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:13
  • +1ነገ 14:22, 23፤ ሕዝ 6:13
  • +ዘፀ 34:15፤ ሕዝ 16:15, 16

ኤርምያስ 2:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:17፤ መዝ 80:8፤ ኢሳ 5:1
  • +ኢሳ 5:4

ኤርምያስ 2:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ለማጠብ የሚያገለግል ንጥረ ነገር።

  • *

    ወይም “ሳሙና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 16:17

ኤርምያስ 2:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሷ በምኞት ስትቃጠል።”

  • *

    ቃል በቃል “በወሯ።”

ኤርምያስ 2:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከባዕዳን አማልክት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 18:12
  • +ኢሳ 2:6፤ ኤር 3:13
  • +ኤር 44:17

ኤርምያስ 2:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 9:7

ኤርምያስ 2:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 44:13
  • +2ዜና 29:6፤ ኤር 32:33
  • +መሳ 10:13-15፤ መዝ 78:34፤ 106:47፤ ኢሳ 26:16፤ ሆሴዕ 5:15

ኤርምያስ 2:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:37, 38
  • +ኤር 11:13

ኤርምያስ 2:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 5:1፤ 9:2፤ ዳን 9:11

ኤርምያስ 2:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:20-22፤ ኢሳ 9:13
  • +ኢሳ 1:5፤ ኤር 5:3፤ ሶፎ 3:2
  • +2ዜና 36:15, 16፤ ነህ 9:26፤ ሥራ 7:52

ኤርምያስ 2:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:15

ኤርምያስ 2:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሙሽሪትስ የሠርጓን መቀነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:21፤ ኢሳ 17:10፤ ኤር 18:15፤ ሆሴዕ 8:14

ኤርምያስ 2:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 33:9

ኤርምያስ 2:34

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በንጹሐን ድሆች ነፍሳት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:16፤ መዝ 106:38፤ ኢሳ 10:1, 2፤ ማቴ 23:35
  • +ዘፀ 22:2

ኤርምያስ 2:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:20, 21
  • +ኢሳ 30:3፤ ኤር 37:7

ኤርምያስ 2:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 13:19

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 2:2ሆሴዕ 2:15
ኤር. 2:2ዘፀ 24:3
ኤር. 2:2ዘዳ 2:7
ኤር. 2:3ዘፀ 19:6፤ ዘዳ 7:6
ኤር. 2:3ዘፀ 17:8, 13
ኤር. 2:5ዘዳ 32:21
ኤር. 2:5መዝ 115:4, 8
ኤር. 2:5ኢሳ 5:4፤ ሚክ 6:3
ኤር. 2:6ዘፀ 14:30
ኤር. 2:6ዘዳ 1:1፤ 32:9, 10
ኤር. 2:6ዘዳ 8:14, 15
ኤር. 2:7ዘኁ 13:26, 27፤ ዘዳ 6:10, 11፤ 8:7-9
ኤር. 2:7ዘሌ 18:24፤ ዘኁ 35:33፤ መዝ 78:58፤ 106:38፤ ኤር 16:18
ኤር. 2:81ሳሙ 2:12፤ ሰቆ 4:13
ኤር. 2:8ሕዝ 34:7, 8
ኤር. 2:81ነገ 18:19፤ ኤር 23:13
ኤር. 2:9ሕዝ 20:35፤ ሚክ 6:2
ኤር. 2:10ዘፍ 10:2, 4
ኤር. 2:10ዘፍ 25:13፤ መዝ 120:5፤ ኤር 49:28
ኤር. 2:11መዝ 106:20
ኤር. 2:13መዝ 36:9፤ ኤር 17:13፤ ራእይ 22:1
ኤር. 2:15ኢሳ 5:29፤ ኤር 4:7
ኤር. 2:16ኤር 46:19
ኤር. 2:16ኤር 43:4, 7፤ 46:14፤ ሕዝ 30:18
ኤር. 2:171ዜና 28:9፤ 2ዜና 7:19, 20
ኤር. 2:18ኢሳ 30:2፤ 31:1፤ ሰቆ 5:6፤ ሕዝ 16:26፤ 17:15
ኤር. 2:182ነገ 16:7፤ ሆሴዕ 5:13
ኤር. 2:19ኤር 4:18
ኤር. 2:19ኤር 5:22
ኤር. 2:20ዘሌ 26:13
ኤር. 2:201ነገ 14:22, 23፤ ሕዝ 6:13
ኤር. 2:20ዘፀ 34:15፤ ሕዝ 16:15, 16
ኤር. 2:21ዘፀ 15:17፤ መዝ 80:8፤ ኢሳ 5:1
ኤር. 2:21ኢሳ 5:4
ኤር. 2:22ኤር 16:17
ኤር. 2:25ኤር 18:12
ኤር. 2:25ኢሳ 2:6፤ ኤር 3:13
ኤር. 2:25ኤር 44:17
ኤር. 2:26ዕዝራ 9:7
ኤር. 2:27ኢሳ 44:13
ኤር. 2:272ዜና 29:6፤ ኤር 32:33
ኤር. 2:27መሳ 10:13-15፤ መዝ 78:34፤ 106:47፤ ኢሳ 26:16፤ ሆሴዕ 5:15
ኤር. 2:28ዘዳ 32:37, 38
ኤር. 2:28ኤር 11:13
ኤር. 2:29ኤር 5:1፤ 9:2፤ ዳን 9:11
ኤር. 2:302ዜና 28:20-22፤ ኢሳ 9:13
ኤር. 2:30ኢሳ 1:5፤ ኤር 5:3፤ ሶፎ 3:2
ኤር. 2:302ዜና 36:15, 16፤ ነህ 9:26፤ ሥራ 7:52
ኤር. 2:31ዘዳ 32:15
ኤር. 2:32መዝ 106:21፤ ኢሳ 17:10፤ ኤር 18:15፤ ሆሴዕ 8:14
ኤር. 2:332ዜና 33:9
ኤር. 2:342ነገ 21:16፤ መዝ 106:38፤ ኢሳ 10:1, 2፤ ማቴ 23:35
ኤር. 2:34ዘፀ 22:2
ኤር. 2:362ዜና 28:20, 21
ኤር. 2:36ኢሳ 30:3፤ ኤር 37:7
ኤር. 2:372ሳሙ 13:19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 2:1-37

ኤርምያስ

2 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “ሂድና ኢየሩሳሌም ጆሮዋ እየሰማ ይህን አውጅ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“በወጣትነትሽ ጊዜ ለአምላክ ያደርሽ እንደነበርሽ፣*+

ደግሞም ለጋብቻ በታጨሽበት ጊዜ ያሳየሽውን ፍቅር፣+

ዘር በማይዘራበት ምድር፣ በምድረ በዳ

እንዴት እንደተከተልሽኝ በሚገባ አስታውሳለሁ።+

 3 እስራኤል ለይሖዋ የተቀደሰ፣+ የመከሩ በኩር ነበር።”’

‘እሱን የሚውጥ ሁሉ በደለኛ ይሆናል።

በእነሱም ላይ ጥፋት ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”+

 4 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ፣

የይሖዋን ቃል ስሙ።

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“አባቶቻችሁ ከእኔ እጅግ የራቁት፣

ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የተከተሉትና+

እነሱ ራሳቸው ከንቱ የሆኑት+ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?+

 6 እነሱ ‘ከግብፅ ምድር ያወጣን፣+

በምድረ በዳ፣ በረሃማ በሆነና+

ጉድጓድ ባለበት ምድር፣

በድርቅ በተጠቃና+ ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ምድር

እንዲሁም ማንም ሰው በማይጓዝበትና

ሰው በማይኖርበት ምድር

የመራን ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም።

 7 በዚያን ጊዜ እኔ ፍሬዋንና በውስጧ ያሉትን ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንድትበሉ

የፍራፍሬ ዛፎች ወዳሉባት ምድር አመጣኋችሁ።+

እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤

ርስቴንም አስጸያፊ ነገር አደረጋችሁት።+

 8 ካህናቱ ‘ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤+

ሕጉ በአደራ የተሰጣቸውም እኔን አላወቁም፤

እረኞቹ በእኔ ላይ ዓመፁ፤+

ነቢያቱ በባአል ስም ትንቢት ተናገሩ፤+

ምንም ጥቅም የማያስገኙላቸውንም አማልክት ተከተሉ።

 9 ‘በመሆኑም ከእናንተ ጋር ገና እሟገታለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤

‘ከልጅ ልጆቻችሁም ጋር እሟገታለሁ።’

10 ‘እስቲ ወደ ኪቲም+ የባሕር ዳርቻዎች* ተሻግራችሁ ተመልከቱ።

አዎ፣ መልእክተኞችን ወደ ቄዳር+ ልካችሁ ጉዳዩን በጥሞና መርምሩ፤

እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሞ እንደሆነ እዩ።

11 አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ?

የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።+

12 እናንተ ሰማያት በዚህ ተደነቁ፤

በታላቅ ድንጋጤም ተርበትበቱ’ ይላል ይሖዋ፤

13 ‘ምክንያቱም ሕዝቤ ሁለት መጥፎ ነገሮች ፈጽመዋል፦

የሕያው ውኃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተው+

የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ይኸውም ውኃ መያዝ የማይችሉና የሚያፈሱ

የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።’*

14 ‘እስራኤል፣ አገልጋይ ወይም የቤት ውልድ ባሪያ ነው?

ታዲያ እንዲበዘበዝ የተደረገው ለምንድን ነው?

15 ደቦል አንበሶች በእሱ ላይ አገሡ፤+

በኃይለኛ ድምፅ ጮኹበት።

ምድሩን የሚያስፈራ ቦታ አደረጉት።

ከተሞቹ ማንም እንዳይኖርባቸው በእሳት ተቃጠሉ።

16 የኖፍና*+ የጣፍነስ+ ሕዝቦች፣ መሃል አናትሽን ይበላሉ።

17 አምላክሽ ይሖዋ በመንገዱ በመራሽ ወቅት

እሱን በመተው+

ይህን በራስሽ ላይ አላመጣሽም?

18 ደግሞስ የሺሆርን ውኃዎች* ለመጠጣት

ወደ ግብፅ የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?+

የወንዙን* ውኃዎች ለመጠጣት

ወደ አሦር የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?+

19 ከክፋትሽ ትምህርት ልታገኚ ይገባል፤

ታማኝነት በማጉደል የፈጸምሻቸው ድርጊቶችም ወቀሳ ያስከትሉብሻል።

አምላክሽን ይሖዋን መተውሽ

መጥፎና መራራ እንደሆነ ማወቅና መገንዘብ ይኖርብሻል፤+

እኔን ፈጽሞ አልፈራሽም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ።

20 ‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤+

የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ።

አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤

ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይና ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር+

ለማመንዘር ተንጋለሽ ተኝተሻልና።+

21 እኔ፣ እንደ ምርጥ ቀይ የወይን ተክል፣ ሙሉ በሙሉ ንጹሕ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤+

ታዲያ በፊቴ እንዲህ ተለውጠሽ የተበላሸ ባዕድ የወይን ተክል የሆንሽው እንዴት ነው?’+

22 ‘በሶዳ* ብትታጠቢና ብዛት ያለው እንዶድ* ብትጠቀሚ እንኳ

ከበደልሽ የተነሳ ዕድፍሽ በፊቴ ይኖራል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

23 ‘ራሴን አላረከስኩም።

ባአልንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ?

በሸለቆው ውስጥ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ።

ያደረግሽውን ነገር ልብ በይ።

በመንገዷ ላይ ወዲያና ወዲህ እንደምትፋንን

የደረሰች ፈጣን ግመል ነሽ፤

24 በምድረ በዳ መኖር እንደለመደች፣

በፍትወቷ* ነፋሱን እንደምታነፈንፍ የዱር አህያ ነሽ።

ስሜቷ ሲነሳሳ ማን ሊመልሳት ይችላል?

የሚፈልጓት ሁሉ እሷን ለማግኘት ብዙ ድካም አይጠይቅባቸውም።

በመራቢያዋ ወቅት* ያገኟታል።

25 እግርሽ እስኪነቃ አትዙሪ፤

ጉሮሮሽም በውኃ ጥም አይቃጠል።

አንቺ ግን ‘አይሆንም! ምንም ተስፋ የሌለው ነገር ነው!+

እኔ ከባዕዳን* ጋር ፍቅር ይዞኛል፤+

እነሱንም እከተላለሁ’ አልሽ።+

26 ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍር፣

የእስራኤል ቤት ሰዎችም እንዲሁ አፍረዋል፤

እነሱም ሆኑ ነገሥታታቸው፣ መኳንንታቸው፣

ካህናታቸውና ነቢያታቸው ውርደት ተከናንበዋል።+

27 ዛፉን ‘አንተ አባቴ ነህ’፤+

ድንጋዩንም ‘የወለድከኝ አንተ ነህ’ ይላሉ።

ለእኔ ግን ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጥተውኛል።+

ጥፋት ሲመጣባቸውም

‘ተነስተህ አድነን!’ ይላሉ።+

28 ለራስህ የሠራሃቸው አማልክት ታዲያ የት አሉ?+

ጥፋት ሲደርስብህ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ ይነሱ፤

ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና።+

29 ‘አሁንም ከእኔ ጋር የምትሟገቱት ለምንድን ነው?

ሁላችሁም በእኔ ላይ ያመፃችሁት ለምንድን ነው?’+ ይላል ይሖዋ።

30 ልጆቻችሁን የመታሁት በከንቱ ነው።+

ለመታረም ፈቃደኞች አይደሉም፤+

የገዛ ራሳችሁ ሰይፍ እንደሚያደባ አንበሳ

ነቢያታችሁን በልቷል።+

31 የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ልብ በሉ።

እኔ ለእስራኤል፣ እንደ ምድረ በዳ

ወይም ድቅድቅ ጨለማ እንደዋጠው ምድር ሆኛለሁ?

የእኔ ሕዝብ የሆኑት እነዚህ ሰዎች ‘እኛ ወደፈለግንበት እንሄዳለን።

ከእንግዲህ ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላሉ?+

32 ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣

ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን* ትረሳለች?

የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።+

33 አንቺ ሴት፣ ፍቅረኛ ለማግኘት መንገድሽን ምንኛ በጥበብ አመቻቸሽ!

የክፋትን መንገዶች ተምረሻል።+

34 ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች* ደም ቆሽሸዋል፤+

ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤

ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።+

35 አንቺ ግን ‘እኔ ንጹሕ ነኝ።

በእርግጥ ቁጣው ከእኔ ተመልሷል’ ትያለሽ።

‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ስለምትዪ፣

በአንቺ ላይ ፍርድ አመጣለሁ።

36 መንገድሽን በመለዋወጥ የምትፈጽሚውን ድርጊት አቅልለሽ የምትመለከቺው ለምንድን ነው?

በአሦር እንዳፈርሽ ሁሉ+

በግብፅም ታፍሪያለሽ።+

37 በዚህም የተነሳ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፤+

ይሖዋ የምትተማመኚባቸውን ነገሮች አስወግዷልና፤

እነሱ ለስኬት አያበቁሽም።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ