7 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መልካም ወደሆነች ምድር ሊያስገባህ ነው፤+ ይህች ምድር ጅረቶች ያሏት፣ በሸለቋማ ሜዳዋና በተራራማ አካባቢዋ ምንጮች የሚፈልቁባትና ውኃዎች የሚንዶለዶሉባት፣ 8 ስንዴ፣ ገብስ፣ ወይን፣ በለስና ሮማን+ የሚበቅልባት፣ የወይራ ዘይትና ማር የሚገኝባት፣+ 9 የምግብ እጥረት የሌለባት፣ ምንም ነገር የማታጣባት፣ ብረት ያለባቸው ድንጋዮች የሚገኙባት እንዲሁም ከተራሮቿ መዳብ ቆፍረህ የምታወጣባት ምድር ናት።