-
ዘዳግም 13:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 “አንድ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ከመካከልህ ተነስቶ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር እንደሚያሳይ ቢነግርህና 2 የነገረህ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር ቢፈጸም፣ እሱም ‘ሌሎች አማልክትን እንከተል’ ይኸውም አንተ የማታውቃቸውን አማልክት እንከተል፤ ‘እናገልግላቸውም’ ቢልህ፣ 3 የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል እንዳትሰማ፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* አምላካችሁን ይሖዋን ትወዱት+ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ እየፈተናችሁ ነው።+ 4 እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ።+ 5 ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ግን ይገደል፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ዞር እንድትሉ፣ ከግብፅ ምድር ባወጣችሁና ከባርነት ቤት በታደጋችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እንድታምፁ አበረታቷችኋል። አንተም ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።+
-
-
ዘዳግም 18:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 “‘እኔ እንዲናገር ያላዘዝኩትን ቃል በእብሪት ተነሳስቶ በስሜ የሚናገር ወይም በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ካለ ያ ነቢይ ይገደል።+
-