-
2 ነገሥት 9:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ኢዩም ቀስቱን አስፈንጥሮ ኢዮራምን በትከሻዎቹ መካከል ወጋው፤ ቀስቱም በልቡ በኩል ወጣ፤ ኢዮራምም እዚያው ጦር ሠረገላው ውስጥ ወደቀ።
-
-
2 ነገሥት 10:6, 7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ከዚያም ኢዩ “የእኔ ከሆናችሁና እኔን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ከሆናችሁ የጌታችሁን ወንዶች ልጆች ራስ ቆርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ይዛችሁልኝ ኑ” የሚል ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈላቸው።
በዚህ ጊዜ 70ዎቹ የንጉሡ ልጆች አሳዳጊዎቻቸው ከሆኑት ታዋቂ የከተማዋ ሰዎች ጋር ነበሩ። 7 እነሱም ደብዳቤው እንደደረሳቸው 70ዎቹን የንጉሡን ልጆች ወስደው አረዷቸው፤+ ከዚያም ጭንቅላታቸውን በቅርጫቶች ውስጥ አድርገው ወደ ኢይዝራኤል ላኩለት።
-
-
2 ነገሥት 10:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ከዚያም ኢዩና የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ+ ወደ ባአል ቤት ገቡ። የባአልንም አምላኪዎች “ከባአል አምላኪዎች በስተቀር አንድም የይሖዋ አምላኪ እዚህ አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” አላቸው።
-