2 ሳሙኤል 8:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በኤዶምም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን ከማቋቋሙም ሌላ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ።+ ይሖዋም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።*+ 2 ነገሥት 8:20-22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 በእሱ ዘመን ኤዶም በይሁዳ ላይ ዓምፆ+ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።+ 21 በመሆኑም ኢዮራም ሠረገሎቹን ሁሉ ይዞ ወደ ጻኢር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እሱንና የሠረገሎቹን አዛዦች ከበው የነበሩትን ኤዶማውያን ድል አደረገ፤ ሠራዊቱም ሸሽቶ ወደየድንኳኑ ሄደ። 22 ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም+ በዚሁ ጊዜ ዓመፀ። መዝሙር 108:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+ በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+ በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+
14 በኤዶምም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን ከማቋቋሙም ሌላ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ።+ ይሖዋም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።*+
20 በእሱ ዘመን ኤዶም በይሁዳ ላይ ዓምፆ+ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።+ 21 በመሆኑም ኢዮራም ሠረገሎቹን ሁሉ ይዞ ወደ ጻኢር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እሱንና የሠረገሎቹን አዛዦች ከበው የነበሩትን ኤዶማውያን ድል አደረገ፤ ሠራዊቱም ሸሽቶ ወደየድንኳኑ ሄደ። 22 ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም+ በዚሁ ጊዜ ዓመፀ።