35 ከዚህ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ ክፉ ድርጊት ከፈጸመው ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝያስ ጋር ግንባር ፈጠረ።+ 36 ወደ ተርሴስ+ የሚሄዱ መርከቦችን ለመሥራትም ተሻረኩ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር+ ሠሩ። 37 ይሁን እንጂ የማሬሻ ሰው የሆነው የዶዳዋ ልጅ ኤሊዔዘር “ከአካዝያስ ጋር ግንባር በመፍጠርህ ይሖዋ ሥራህን ያፈርሰዋል” ሲል በኢዮሳፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ።+ በመሆኑም መርከቦቹ ተሰባበሩ፤+ ወደ ተርሴስም መሄድ ሳይችሉ ቀሩ።