-
ዘዳግም 3:13-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 የቀረውን የጊልያድን ክፍልና በኦግ ግዛት ሥር ያለውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ።+ የባሳን ይዞታ የሆነው የአርጎብ አካባቢ በሙሉ የረፋይም ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር።
14 “የምናሴ ልጅ ያኢር+ የአርጎብን ክልል+ በሙሉ እስከ ገሹራውያን እና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ ያለውን ወሰደ፤ በባሳን የሚገኙትን እነዚህን መንደሮች በራሱ ስም ሃዎትያኢር*+ ብሎ ሰየማቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሚጠሩት በዚህ ስም ነው። 15 ጊልያድን ደግሞ ለማኪር ሰጠሁት።+ 16 ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን+ የአርኖንን ሸለቆ* መሃል ወሰን በማድረግ ከጊልያድ አንስቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ እንዲሁም የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው ሸለቆ ማለትም እስከ ያቦቅ ድረስ ሰጠኋቸው፤
-
-
ዘዳግም 28:63አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
63 “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ።
-
-
ኢያሱ 13:8-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 የተቀረው የምናሴ ነገድ እኩሌታና ሮቤላውያን እንዲሁም ጋዳውያን የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በሰጣቸው መሠረት ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ርስታቸውን ወስደዋል፤+ 9 ይህም በአርኖን ሸለቆ*+ መካከል የምትገኘውን ከተማና የመደባን አምባ በሙሉ ጨምሮ በሸለቆው ዳርቻ ላይ ከምትገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ዲቦን ድረስ ያለውን አካባቢ፣ 10 በሃሽቦን ሆኖ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ከተሞች በሙሉ እስከ አሞናውያን+ ወሰን ድረስ፣ 11 ጊልያድን፣ የገሹራውያንንና የማአካታውያንን+ ግዛት፣ የሄርሞንን ተራራ በሙሉ፣ ባሳንን+ በሙሉ እስከ ሳልካ+ ድረስ 12 እንዲሁም በአስታሮት እና በኤድራይ ሆኖ ይገዛ የነበረውን በባሳን ያለውን የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ ያጠቃልላል። (እሱም በሕይወት ከተረፉት የመጨረሻዎቹ የረፋይም ዘሮች አንዱ ነበር።)+ ሙሴም ድል አድርጎ አባረራቸው።+
-