-
2 ዜና መዋዕል 23:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ድፍረት የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ከመቶ አለቆቹ+ ይኸውም ከየሮሃም ልጅ ከአዛርያስ፣ ከየሆሃናን ልጅ ከእስማኤል፣ ከኢዮቤድ ልጅ ከአዛርያስ፣ ከአዳያህ ልጅ ከማአሴያህ እና ከዚክሪ ልጅ ከኤሊሻፋጥ ጋር ስምምነት* አደረገ። 2 ከዚያም በይሁዳ ሁሉ በመዘዋወር ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሌዋውያንንና+ የእስራኤልን የአባቶች ቤት መሪዎች ሰበሰቡ። ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ 3 መላው ጉባኤ በእውነተኛው አምላክ ቤት ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን ገባ፤+ ከዚያም ዮዳሄ እንዲህ አላቸው፦
“እነሆ፣ ይሖዋ የዳዊትን ወንዶች ልጆች አስመልክቶ ቃል በገባው መሠረት የንጉሡ ልጅ ይገዛል።+
-