-
2 ዜና መዋዕል 23:4-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 እናንተም እንዲህ ታደርጋላችሁ፦ በሰንበት ቀን ተረኛ ከሚሆኑት ካህናትና ሌዋውያን+ መካከል አንድ ሦስተኛዎቹ በር ጠባቂዎች ይሆናሉ፤+ 5 አንድ ሦስተኛዎቹ ደግሞ በንጉሡ ቤት*+ ይሆናሉ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ በመሠረት በር ላይ ይሆናል፤ ሕዝቡ ሁሉ ደግሞ በይሖዋ ቤት ግቢዎች+ ውስጥ ይሆናል። 6 ከሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን በስተቀር ማንንም ወደ ይሖዋ ቤት እንዳታስገቡ።+ እነሱ የተቀደሱ ስለሆኑ ይግቡ፤ የቀረውም ሕዝብ ሁሉ ለይሖዋ ያለበትን ግዴታ ይፈጽማል። 7 ሌዋውያኑም እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን ዙሪያውን ይክበቡት። ወደ ቤቱም ውስጥ የሚገባ ማንኛውም ሰው ይገደላል። ንጉሡ በሚሄድበት ሁሉ* አብራችሁት ሁኑ።”
-