-
2 ነገሥት 11:5-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “እናንተም እንዲህ ታደርጋላችሁ፦ ከመካከላችሁ አንድ ሦስተኛ የምትሆኑት በሰንበት ቀን ገብታችሁ የንጉሡን ቤት*+ በተጠንቀቅ ትጠብቃላችሁ፤ 6 አንድ ሦስተኛ የምትሆኑት ደግሞ በመሠረት በር ላይ ትሆናላችሁ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ ከቤተ መንግሥቱ ዘቦች ኋላ ባለው በር ላይ ይሆናል። ቤቱን በየተራ ትጠብቃላችሁ። 7 ከመካከላችሁ በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ንጉሡን ከጥቃት ለመከላከል የይሖዋን ቤት በተጠንቀቅ ይጠብቁ። 8 እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ንጉሡን ዙሪያውን ክበቡት። ረድፉን ጥሶ የገባ ማንኛውም ሰው ይገደላል። ንጉሡ በሚሄድበት ሁሉ* አብራችሁት ሁኑ።”
-
-
1 ዜና መዋዕል 9:22-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 በደጆቹ ላይ ቆመው እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ 212 ነበሩ። እነሱም በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት+ በሰፈሮቻቸው ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዳዊትና ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል እነዚህን ሰዎች ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ሾሟቸው። 23 እነሱና ወንዶች ልጆቻቸው የይሖዋን ቤት ይኸውም የማደሪያ ድንኳኑን* በሮች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 24 በር ጠባቂዎቹ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ በኩል ነበሩ።+ 25 በየሰፈሮቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻቸው ለሰባት ቀናት አብረዋቸው ለማገልገል አልፎ አልፎ ይመጡ ነበር።
-