-
2 ዜና መዋዕል 23:18-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ከዚያም ዮዳሄ በይሖዋ ቤት የሚከናወኑትን ሥራዎች እንዲቆጣጠሩ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሾመ፤ እነሱም በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው+ እንዲሁም ዳዊት ባዘዘው መሠረት* በደስታና በመዝሙር ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት በይሖዋ ቤት በየምድቡ የመደባቸው ናቸው።+ 19 በተጨማሪም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ በር ጠባቂዎቹን+ በይሖዋ ቤት በሮች ላይ አቆመ። 20 ከዚያም መቶ አለቆቹን፣+ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዢዎችና የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ፤ ንጉሡንም አጅበው ከይሖዋ ቤት ወደ ታች አመጡት። በላይኛውም በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት* ገቡ፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ+ ዙፋን+ ላይ አስቀመጡት። 21 በመሆኑም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እጅግ ተደሰተ፤ ጎቶልያንም በሰይፍ ስለገደሏት ከተማዋ ጸጥታ ሰፈነባት።
-