-
2 ነገሥት 22:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 “ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ+ ሂድ፤ በር ጠባቂዎቹ ከሕዝቡ ላይ የሰበሰቡትንና ወደ ይሖዋ ቤት የገባውን ገንዘብ በአጠቃላይ እንዲሰበስብ አድርግ።+ 5 ገንዘቡን በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች ይስጧቸው፤ እነሱ ደግሞ በይሖዋ ቤት ውስጥ የፈረሰውን* ለሚጠግኑት ሠራተኞች ይስጡ፤+ 6 ይኸውም ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ፣ ለግንባታ ባለሙያዎቹና ለግንበኞቹ ያስረክቡ፤ እነሱም ገንዘቡን ለቤቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ጥርብ ድንጋዮች ለመግዛት ይጠቀሙበታል።+
-
-
2 ዜና መዋዕል 24:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 ከዚያም ንጉሡና ዮዳሄ ገንዘቡን በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ለሚቆጣጠሩት ሰዎች ይሰጧቸው ነበር፤ እነሱ ደግሞ የይሖዋን ቤት ለማደስ+ ድንጋይ ጠራቢዎችንና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን እንዲሁም የይሖዋን ቤት ለመጠገን የብረትና የመዳብ ሠራተኞችን ይቀጥሩ ነበር።
-