4 ኢዮዓስ ካህናቱን እንዲህ አላቸው፦ “ቅዱስ መባ+ ሆኖ ወደ ይሖዋ ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ ማለትም እያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅበትን ገንዘብ፣+ አንድ ሰው እንዲከፍል የተተመነበትን ገንዘብና እያንዳንዱ ሰው ልቡ አነሳስቶት ወደ ይሖዋ ቤት የሚያመጣውን ገንዘብ በሙሉ ውሰዱ።+ 5 ካህናቱ በግል ቀርበው ገንዘቡን ከለጋሾቻቸው ላይ መቀበል ይችላሉ፤ ከዚያም በቤቱ ውስጥ የፈረሰውን ሁሉ ለመጠገን ይጠቀሙበት።”+