3 የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን “ራሞትጊልያድ+ የእኛ እንደሆነች ታውቃላችሁ አይደል? ሆኖም እሷን ከሶርያ ንጉሥ እጅ ለማስመለስ እያመነታን ነው” አላቸው። 4 ከዚያም ኢዮሳፍጥን “በራሞትጊልያድ ለመዋጋት ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ?” አለው። በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ለእስራኤል ንጉሥ “እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ። ሕዝቤ ሕዝብህ ነው። የእኔ ፈረሶችም የአንተ ፈረሶች ናቸው” በማለት መለሰለት።+