ሆሴዕ 13:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ሰማርያ በአምላኳ ላይ ስላመፀች+ ተጠያቂ ትሆናለች።+ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ልጆቻቸው ይፈጠፈጣሉ፤የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።” አሞጽ 3:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ጠላት ምድሪቱን ይከባል፤+ብርታትሽን ያሟጥጣል፤የማይደፈሩ ማማዎችሽም ይበዘበዛሉ።’+ ሚክያስ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የፍርስራሽ ክምር፣ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፤*መሠረቶቿንም አራቁታለሁ።