-
2 ዜና መዋዕል 33:2-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 እሱም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ልማዶች በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 3 አባቱ ሕዝቅያስ አፍርሷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፣+ ለባአል አማልክት መሠዊያዎችን አቆመ፣ የማምለኪያ ግንዶች* ሠራ እንዲሁም ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።+ 4 በተጨማሪም ይሖዋ “ኢየሩሳሌም ለዘላለም በስሜ ትጠራለች”+ ብሎ በተናገረለት በይሖዋ ቤት ውስጥ መሠዊያዎችን ሠራ።+ 5 ደግሞም በይሖዋ ቤት በሚገኙት በሁለቱ ግቢዎች ውስጥ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።+ 6 በሂኖም ልጅ ሸለቆም+ የገዛ ልጆቹን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤+ አስማተኛ፣+ ሟርተኛና መተተኛ ሆነ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ።+ ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ።
-
-
2 ዜና መዋዕል 36:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ዋነኞቹ ካህናት ሁሉና ሕዝቡ፣ ብሔራት የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ነገሮች በማድረግ እጅግ ከፍተኛ ክህደት ፈጸሙ፤ ይሖዋ በኢየሩሳሌም የቀደሰውንም ቤት አረከሱ።+
-