የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 5:7-9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ከእኔ በቀር* ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።+

      8 “‘በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸ ቅርጽም+ ሆነ የተሠራ ምስል ለራስህ አታብጅ። 9 ለእነሱ አትስገድ፤ አታገልግላቸውም፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤+

  • መሳፍንት 2:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 እነሱ ግን መሳፍንቱን እንኳ ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ እንዲያውም ከሌሎች አማልክት ጋር አመነዘሩ፤ ለእነሱም ሰገዱ። የይሖዋን ትእዛዛት ያከብሩ የነበሩ አባቶቻቸው ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ዞር አሉ።+ እነሱ እንዳደረጉት ማድረግ ሳይችሉ ቀሩ።

  • መሳፍንት 8:33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 እስራኤላውያን ጌድዮን ከሞተ ብዙም ሳይቆይ እንደገና ከባአል ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ፤+ ባአልበሪትንም አምላካቸው አደረጉት።+

  • 2 ነገሥት 17:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በእያንዳንዱ ኮረብታ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር+ የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው አቆሙ፤ 11 ይሖዋ ከፊታቸው አሳዶ በግዞት እንዲወሰዱ ያደረጋቸው ብሔራት ያደርጉ እንደነበረው ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ሁሉ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።+ ይሖዋን ለማስቆጣት ክፉ ነገሮችን ማድረጋቸውን ቀጠሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ