15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መግዛቱን ቀጠለ፤+ ለሕዝቡም ሁሉ+ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።+ 16 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ+ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር። 17 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅና+ የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሰራያህ ደግሞ ጸሐፊ ነበር። 18 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ የከሪታውያንና የጴሌታውያን+ አዛዥ ነበር። የዳዊት ወንዶች ልጆችም ዋና ኃላፊዎች ሆኑ።