-
1 ሳሙኤል 16:6-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 እነሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤልያብን+ ሲያየው “መቼም ይሖዋ የሚቀባው ሰው ይህ መሆን አለበት” አለ። 7 ሆኖም ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “እኔ ስላልተቀበልኩት መልኩንና የቁመቱን ርዝማኔ አትይ።+ አምላክ የሚያየው ሰው በሚያይበት መንገድ አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው፤ ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው።”+ 8 ከዚያም እሴይ አቢናዳብን+ ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ እሱ ግን “ይሄኛውንም ይሖዋ አልመረጠውም” አለ። 9 ቀጥሎም እሴይ ሻማህ+ እንዲቀርብ አደረገ፤ እሱ ግን “ይሄኛውንም ይሖዋ አልመረጠውም” አለ። 10 በመሆኑም እሴይ ሰባቱም ወንዶች ልጆቹ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን እሴይን “ይሖዋ ከእነዚህ መካከል ማናቸውንም አልመረጠም” አለው።
-