-
2 ነገሥት 21:19-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 አምዖን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሁለት ዓመት ገዛ።+ እናቱ ሜሹሌሜት ትባል ነበር፤ እሷም የዮጥባ ሰው የሆነው የሃሩጽ ልጅ ነበረች። 20 አምዖን አባቱ ምናሴ እንዳደረገው በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 21 አባቱ በሄደበት መንገድ ሁሉ ተመላለሰ፤ ደግሞም አባቱ ያገለግላቸው የነበሩትን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች አገለገለ፤ ለእነሱም ሰገደ።+ 22 የአባቶቹንም አምላክ ይሖዋን ተወ፤ በይሖዋም መንገድ አልሄደም።+ 23 ከጊዜ በኋላም የንጉሥ አምዖን አገልጋዮች በእሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት። 24 ሆኖም የምድሪቱ ሕዝብ በንጉሥ አምዖን ላይ ያሴሩትን ሁሉ ገደላቸው፤ በእሱም ምትክ ልጁን ኢዮስያስን አነገሠው።+
-