ዘዳግም 30:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና+ ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው+ 18 በእርግጥ እንደምትጠፉ+ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል። ዘዳግም 31:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+ ዘዳግም 31:24-26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ+ እንደጨረሰ 25 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። ኢያሱ 1:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤+ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤*+ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።+
17 “ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና+ ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው+ 18 በእርግጥ እንደምትጠፉ+ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል።
16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+
24 ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ+ እንደጨረሰ 25 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል።
8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤+ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤*+ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።+