-
1 ነገሥት 14:25-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ+ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ።+ 26 እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ።+ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ።+ 27 በመሆኑም ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ* አለቆች ሰጣቸው። 28 ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር።
-