-
ዘፍጥረት 18:23-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ከዚያም አብርሃም ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር አብረህ ታጠፋለህ?+ 24 እስቲ በከተማዋ ውስጥ 50 ጻድቅ ሰዎች አሉ እንበል። ታዲያ ሁሉንም ዝም ብለህ ታጠፋቸዋለህ? በውስጧ ስለሚኖሩት 50 ጻድቃን ስትል ስፍራውን አትምርም? 25 በጻድቁም ሆነ በኃጢአተኛው ላይ ተመሳሳይ ነገር እንዲደርስ የሚያደርግ እንዲህ ዓይነት እርምጃ በመውሰድ ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ላይ ትገድላለህ ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው!+ ይህ በአንተ ዘንድ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው።+ የምድር ሁሉ ዳኛ ትክክል የሆነውን ነገር አያደርግም?”+
-
-
1 ነገሥት 14:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ልጅ አቢያህ ታመመ።
-
-
1 ነገሥት 14:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ከኢዮርብዓም ቤተሰብ መካከል በመቃብር ቦታ የሚቀበረው እሱ ብቻ ስለሆነ እስራኤል ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ አንድ መልካም ነገር ያገኘበት እሱን ብቻ ነው።
-